
ለማመልከቻው ፋይል ለማድረግ የሚያስችል መረጃ
ዜግነት/ ናቹራይዜሽን ማመልከቻ

የዜግነት አመልካቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ሊኖራቸው ይገባል.
-
ኦሪጅናል አረንጓዴ ካርድ
-
ሁለት የፓስፖርት መጠን ፎቶዎች
-
የግዛት መታወቂያ/የመንጃ ፍቃድ
-
ከUS ያደረጉት ጉዞ፡ የመነሻ ቀን፣ ወር፣ አመት እና የተመለሱበት ቀን፣ ወር እና አመት። ከUS ውጭ የወሰዱ አጠቃላይ ቀናት።
-
የእናት ሙሉ ስም እና የትውልድ ቀን / እሱ / እሷ ዜጋ ከሆነ /
-
የአባት ሙሉ ስም እና የትውልድ ቀን / እሱ / እሷ ዜጋ ከሆነ /
-
ያለፉት አምስት ዓመታት አድራሻ፡ የመግባት እና መውጫ ቀን/ወር/አመት
-
ያለፉት አምስት ዓመታት የቅጥር መረጃ …… የአሰሪ ስም፣ ከ ------ እስከ --- እና የስራ መደቡ
-
የልጆች መረጃ፤ ሙሉ ስም እና የትውልድ ቀን/አረንጓዴ ካርድ…
-
$ 725 የማመልከቻ ክፍያ፣ ወይም የ DSHS ደብዳቤ የቅርብ ቅጂ ካለዎት ክፍያው ሊሰረዝ ይችላል።
-
የጋብቻ የምስክር ወረቀት / ያገባ ከሆነ /
-
የፍቺ የምስክር ወረቀት/ከተፋቱ/
የግሪን ካርድ አመልካቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ሊኖራቸው ይገባል I-485
-
ፎቶግራፎች - ሁለት በቅርብ ጊዜ ተመሳሳይ ቀለም ያለው የፓስፖርት አይነት የራስዎን እና የሚመለከቷቸውን ቤተሰቦች ፎቶግራፎች ማስገባት አለቦት።
-
የሕክምና ምርመራ እና የክትባት መዝገብ (ቅጽ I-693)
-
በመንግስት የተሰጠ የማንነት ሰነድ ከፎቶግራፍ/መታወቂያ/ ጋር
-
የስደተኛ ወይም የጥገኝነት ሁኔታን የሚያሳይ I-94 ሰነድ
-
የጋብቻ የምስክር ወረቀት እና ሌላ የግንኙነት ማረጋገጫ/ ካለ/
-
የልጆች የልደት የምስክር ወረቀት የሁለቱም ወላጆች ስም / ለስደተኞች አስፈላጊ አይደለም.
-
አሁን የምትኖርበት አድራሻ
-
ወደ አሜሪካ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የኖሩበት አድራሻ
-
ከአንድ ዓመት በላይ ከዩናይትድ ስቴትስ ውጭ የኖሩት አድራሻ
-
የልጆችዎ ፣ ስም ፣ ልደት ቀን እና የትውልድ ሀገር መረጃ
-
የገንዘብ ማዘዣ 1,225 ዶላር